Fana: At a Speed of Life!

ከ18 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሪፐብሊካን ጥበቃ የተገነባው መኖሪያ ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በለገዳዲ ሳይት ከ18 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሪፐብሊካን ጥበቃ ያስገነባውን መኖሪያ ቤት አስመረቀ፡፡
የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ እንደተናገሩት ቤቶቹ የመኖሪያ ቤት እጥረትን የሚፈቱ ሲሆኑ፥ ሰራዊቱ የሚሠጠውን ተልዕኮ ፈፅሞ ሲመለስ እንደ ማረፊያ በማገልገል ረገድ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
የመከላከያ መሃንዲስ መምሪያ ተወካይ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ደረጀ መገርሳ በበኩላቸው መጀመር ብቻ ሳይሆንመጨረስንም ባህል በማድረግ የየቤት ግንባታ ተልዕኮውን ባጭር ጊዜ በጥራት በማጠናቀቅ ማስረከባቸውን ተናግረዋል።
ግንባታው ለአንድ ሻለቃ የሰራዊት አባላት መኖሪያ የሚሆኑ መመገቢያ አዳራሽን ጨምሮ የተለያዩ ክፍሎችን ያካተተ ነው፡፡
ከቤቶቹ ርክክብ ጎን ለጎንም ኢትዮጵያን እናልብስ የሚለውን ጥሪ በመቀበል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር መካሄዱን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.