Fana: At a Speed of Life!

ከ180 ሺህ ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖቶችን ባንክ ወስደው ሊቀይሩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ180 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ ገንዘብ ኖቶችን ወደ ንብ ባንክ ወስደው ሊቀይሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሁለቱ ግለሰቦች በህጋዊ ባንክ ስም ተመሳስሎ በተሰራ እና ወደፊት በሚጣራ ቲተር በመጠቀም ከ180 ሺህ ብር በላይ ሃሰተኛ ገንዘብ ወደ ንብ ባንክ ወስደው ሊቀይሩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ግለሰቦቹ የያዙትን ሃሰተኛ ብር ንብ ባንክ ካዛንቺስ ቅርጫፍ ካሉ ሰራተኞች ጋር 40 ከመቶ ለባንክ 60 ከመቶ ለራሳቸው ለማዋል ስምምነት አድርገው ከመኪናቸው አወጥተው ብሩን ሊመነዝሩ ሲሉ በባንኩ ጥቆማ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸም ተገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይንስና ንግድ ነክ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ጋር በተደረገ ክትትል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ከዚያም ባለፈ በቱሉ ዲምቱ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ፍተሻ ተመሳሳይ መጠን ያለው ሃሰተኛ ብር መያዙን ረዳት ኮሚሸነር ብርሃኑ ተናገረዋል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛልም ነው ያሉት።

ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አያይዘውም ባንኮችም ሆኑ ህብረተሰቡ ከአዲሱ ብር ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ማንኛውንም ህገወጥ እንቅስቃሴ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ አሳሰበዋል።

በታሪክ አዱኛ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.