Fana: At a Speed of Life!

ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሁሉም የጉምሩክ ኬላና መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በተደረገ ክትትል ነው 27 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችና 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች ከሀዋሳ ፣ ጅግጅጋ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተያዙት፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች ፣ የምግብ ዘይት ፣ የጦር መሳሪያዎችና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ እና በጥቆማ የተያዙ ሲሆኑ ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የተገኙ 33 ተሽከርካሪዎችም ከዕቃዎቹ ጋር መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.