Fana: At a Speed of Life!

ከ70 በላይ ሀገራት 14 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሪፖርት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ70 በላይ ሀገራት 14 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሪፖርት መደረጉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የቫይረሱ ሥርጭት ሳይታወቅ ከምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ወደ በርካታ የዓለም ሀገራት ሳይሥፋፋ እንዳልቀረም ነው የተጠቆመው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ቴክኒካል መሪ የሆኑት ሮሳመንድ ሉዊስ ÷ ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ከየት እንደተከሰተ ማወቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ለጉዳዩ ምላሽ እንደሌለው ለሲ ኤን ኤን የገለጹት ሮሳመንድ ሉዊስ፥ ከአባል ሀገራት ጋር ወረርሽኙ ይበልጥ ሳይሥፋፋ ለመከላከል እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በርካታ ሕሙማን የሕክምና ክትትል ሳያደርጉ ከሣምንታት በኋላ ማገገም እንደቻሉ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የፈንጣጣ በሽታ መከላከያ ክትባቶች የዝንጀሮ ፈንጣጣንም በመከላከል ረገድ ውጤታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሕጻናትና ወጣቶች በሥፋት የሚሰራጭ ከሆነና በተዛማጅ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎችን ካጠቃ እና የመቀየር ባሕሪ ካሳየ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል መገለጹን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.