Fana: At a Speed of Life!

በአንድ አይሱዙ መኪና የተጫነ ሃሺሽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ አይሱዙ መኪና የተጫነ ሃሺሽ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ሃሺሹ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሻሸመኔ ወደ ኬንያ በመጓጓዝ ላይ እያለ በሀዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በጪጩ ጉምሩክ ጣብያ ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር መያዙ ተገልጿል።

የመኪናው አሽከርካሪ ለፍተሻ ተባባሪ ባለመሆኑ ተረኛ ፌደራል ፖሊስ ጎማውን በጥይት በመምታት በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል።

የተያዘው ሃሺሽም በተገቢው መንገድ እንዲወገድ ለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.