Fana: At a Speed of Life!

ከ4 ሺህ በላይ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ከ4 ሺህ በላይ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበርክተዋል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከወጣቶችና ከስፖርቱ ቤተሰብ ያሰባሰበውን ከ3 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ዛሬ ለቤተ-መጻሕፍቱ አስረክቧል።

የቢሮው ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሠ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ተወካይ አስረክበዋል።

ከመጻሕፍቱ መካከል ከ2 ሺህ በላይ የሚሆነው ከወጣቶች የተሰበሰበ ሲሆን÷ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከስፖርቱ ቤተሰብና ከቢሮ ሰራተኞች የተሰበሰቡ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተመሳሳይ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ከ1ሺህ በላይ የተለያዩ መጽሐፍትን ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አበርክቷል፡፡

የመጻሕፍት ርክክቡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባህል፤ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው በተገኙበት በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ተከናውኗል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.