Fana: At a Speed of Life!

ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ዶላሩና እቃው በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ምሽት ላይ መያዙንም አስታውቋል።

እቃው ኮንቴነር በጫነ ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነድ በመያዝ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያለ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ከተማ ላይ በክልሉ ፖሊስ አባላት እና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር ሊያዝ ችሏል።

የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችም 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና 2 ሚሊየን 184 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ልባሽ ጨርቅ በድምሩ 7 ሚሊየን 784 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው እቃዎች ናቸው።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት መሀመድ አብዱላሂ አብዲ የተባለ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ 26 ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በደወሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውሏል።

መረጃው የገቢዎች ሚኒስቴር ነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.