Fana: At a Speed of Life!

ከ72 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ72 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገ ክትትል 47 ነጥብ 4 ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 24 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ ፣ አዳማ እና ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ፥ በቅደም ተከተል 15 ነጥብ 4 ሚሊየን፣ 12 ሚሊየን እና አምስት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ በጋራ ባደረጉት ጥረት ሲሆን፥ የኮንትባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል የጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ፥ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.