Fana: At a Speed of Life!

ከ750 በላይ የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ ወደየ አካባቢያቸው ሊመለሱ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ750 በላይ የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ህዝባዊ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ ወደየ አካባቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ህይወታቸውን ይመራሉ።
የሕወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት በርካታ የቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎች ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል።
ከነዚህም መካከል በአፋር ክልል አዋሽ አርባ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል 764 የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ የተሃድሶ ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል።
የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የተሃድሶ ስልጠናው አስተባባሪ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ አብዛኛው ሰልጣኞች ከግብርና ስራ ላይ ተገደው ወደ ውጊያ የተሰማሩ አርሶአደሮች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ከፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ በርካቶቹ በፅንፈኛው የሕወሃት ቡድን ጠባብነትና ተገፊነት እኩይ አስተሳስቦች ሰለባ በመሆናቸው የተሃድሶ ስልጠና ማስፈለጉን ገልጸዋል።
በዚህም ወጣቶች የአገራዊ ለውጡን ምንነትና የህግ ማስከበር ሂደት የአቅም ግንባታና የአስተሳስብ ለውጥ ላይ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን አቶ ዘሪሁን ተናግረዋል።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እጅ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ከሎጀስቲክስ ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎ በአዋሽ አርባ የተሐድሶ ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ወደየአካባቢያቸው ተመልሰው ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው መደበኛ ህይወታቸውን ይመራሉ ብለዋል።
ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የተለየ ሁኔታ ጥፋት የፈጸሙ ካልሆኑ በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲደገፉ ይደረጋል ነው ያሉት።
ከመጀመሪያው ምዕራፍ ስልጠና በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ ስልጠናዎች ተሰጥተው በቀጣይ ሶስት ሳምንት ተጠናቆ አባላቱ ወደየ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።
የትይግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል በበኩላቸው÷ እየተሰጠ ያለው ስልጠና የአባላቱን አቅም ለመገንባት፣ ህዝብና አገራቸውን የሚክሱበትና ራሳቸውን የሚለውጡበት እንደሆነ ገልጸዋል።
ስልጠናው በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸው÷ ሲጠናቀቅም በቅርቡ በነጻነት ተንቀሳቅሰው ህይወታቸውን መምራት ይጀምራሉ ብለዋል።
የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ የአገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ፤ እንዲህ አይነት የተሀድሶ ስልጠናውን ላላገኙት ይሰጣልም ነው ያሉት።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.