Fana: At a Speed of Life!

ከ8 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምስት ቀናት ውስጥ 8 ሚሊየን 943 ሺህ 420 ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የብር ጌጣጌጥ በጫማና ሻንጣ ውስጥ በመደበቅ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሞባይል፣ የምግብ ዘይት፣ አልባሳት እና ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሕገ ወጥ ዕቃዎች ተይዘዋል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ድሬዳዋ ቢዮ ቆቤ አካባቢ፣ አዳማ፣ ሞያሌ፣ ሞጆ፣ ባህር ዳር፣ ጅግጅጋ እና በሌሎች የኬላ ጣብያዎች በተደረገ
ቁጥጥርና ፍተሻ መያዛቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኮንትሮባንድ መከላከልና ኢንተለጀንስ ሰራተኞች፣ የፌደራልና ክልል ፖሊሶች እንዲሁም የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጥቆማና ድጋፍ ማድረጋቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.