Fana: At a Speed of Life!

ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በዲጂታል መልክ ትምህርት ለመስጠት ማቀዱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በዲጂታል ትምህርት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በየደረጃው በትምህርት ዘርፉ የ10 ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ጀምረዋል።

እቅዱ ሲተገበር መንግስት ለወረቀትና ህትመት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ያስቀራል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎች ከዲጂታል ዓለሙ ጋር በቀላሉ እንዲቀላቀሉ እንደሚያግዛቸውም ነው የተነሳው፡፡

የትምህርት ዘርፉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አለመደገፍ፣ ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት አለመኖር፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት አለመስፈን በትምህርት ጥራቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገልጿል።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ለማፍራት የሚያስችሉ አሰራሮች በእቅዱ ውስጥ በዋናነት ተካተዋልም ተብሏል።

ወደ ዲጂታል ስርዓቱ ለመግባት ለተማሪዎች ታብሌቶችን ለማሟላት የተለያዩ አማራጮች እየተፈለጉ ነው።

የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.