Fana: At a Speed of Life!

ካሞን17 የተሰኘው የቴክኖሞባይል በኤ አይ በታገዘው የላቀ ፎቶ የማንሳት አቅሙ መሪነቱን አሳየ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ካሞን17 የተሰኘው ቴክኖሞባይል በኤ አይ በታገዘው የላቀ ፎቶ የማንሳት አቅሙ መሪነቱን ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

እንደ ታዋቂው ካውንተር ፖይንት ሪሰርች ኢንስቲቲዩት የቅርብ ጊዜ ሪፖርት መሠረት፤ ቴክኖ ሞባይል ገበያው ላይ ካሉ ጥቂት የዘመናዊ ስልክ አምራች ድርጅቶች መካከል በላቀ የኤ አይ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያለው የቋሚ እና የተንቀሳቃሽ ምስሎችን በተሻለ መልኩ መቅረፅ የሚያስችሉ ስልኮችን ማምረት ከቻሉ ድርጅቶች መካከል ተመድቧል።

በሪፖርቱ የዘመናዊ ስልኮች እና የካሜራ ጥራት እድገት አንዱ በሌላኛው እድገት ላይ የተመረኮዘ ሲሆን፥ ይህም እያደገ ባለው የኤ አይ ቴክኖሎጂ ልህቀት ላይ ይወሰናል ነው የተባለው።

እየጨመረ ያለው የካሜራዎች ጥራት መሻሻል ሂደት ወደ አምስተኛ ትውልድ (5ጂ) ዘመን የሚያሻግር ሲሆን፥ የሰው ልጅ በአይኑ ማየት ከሚችለው ጥራት ጋር መስተካከል የሚችሉ የስልክ ካሜራዎች እስከሚፈበረኩ ድረስ ሂደቱ ይቀጥላልም ነው ያለው በሪፖርቱ።

በአሁኑ ወቅት የኤ አይ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ረጃጅም የመተግበሪያ መመሪያዎችን ማንበብ ሳይጠበቅባቸው ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን በስልካቸው መስራት አስችሏቸዋል።

እንዲሁም ብዙዎች ያለችግር ከጀርባ ያለ አካባቢን ማስወገድ፣ መቀነስ እና ለእይታ እንዳይረብሽ አካባቢን መቀነስ እንዲሁም የሰውነትን አቀማመጥ ወደተፈላጊው ቦታ ማስተካከል ችለዋልም ተብሏል።

ይሄው የቴክኖ ካሞን 17 ስልክ እጅግ ዘመናዊ የሆነውን የTAIVOS ምስል ጥራት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደንበኞች በአስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ሳይቀር ጥሩ ምስሎችን ማንሳት እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው።

በዚሁ በካሞን 17 ላይ የሚገኘው የምሽት ላይ ፎቶ ማንሻ ተጠቃሚዎች ጨለም ባለ ቦታ ላይ ሆነው ማንሳት የሚያስችላቸውን TAIVOS ቴክኖሎጂን ያካተተ ሲሆን፥ ቴክኖሎጂው በ1.3um ካሜራ ዝቅተኛ የብርሃን መጠን ያለውን አካባቢ ጥራቱን ከፍ በማድረግ ጥራት ያለው ፎቶ ማንሳት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

የካውንተር ፖይንት እንደተነበየው የኤ አይ ቴክኖሎጂ የተካተተባቸው ግልጋሎቶች እና ፈጠራዎች ውጤት አምራች የሆኑ ዘመናዊ ስልክ አምራቾች ገበያው ላይ ልዩ የሆኑ ምርቶችን ይዘው እንዲገኙያደርጋቸዋል፡፡

ስልኩ የስምንት ጂቢ ራም እና የ256 ጂቢ ሮም የተገጠመለት ሲሆን፥ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የ5 ሺህ mAh ባትሪ ተገጥሞለታል፡፡

ባትሪው በአሳቻ ሰዓት ላይ ቢያልቅ “የፍላሽ ቻርጅ ቴክኖሎጂ” ያለው ሲሆን ደንበኛው በአጭር ግዜ ውስጥ ቻርጅ ማድረግ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

በአዲሱ ካሞን 17 ስልክ የተካተቱት የሰልፊ ማንሻ ማሻሻያ እና ማከማቻ ግልጋሎቶች ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሞዴሎች በተሻለ የደንበኛውን ፍላጎት ያሟሉ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.