Fana: At a Speed of Life!

ካርበን ሞኖክሳይድ (የከሰል ጭስ) ዝምተኛው ገዳይ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያያዞ አብዛኛዎቻችን ከብርድ ራሳችንን ለመከላከል በቤታችን ውስጥ ከሰል የማጨስ ልምድ አለን፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ቤታችንን ለማሞቅ የምንጠቀምበት ጭስ በአግባቡና በጥንቃቄ ካልያዝነው የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአንጎል ውድመትና ለልብ በሽታ ሊያጋልጥ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ከዘህ ባለፈም ጉዳዩ በጥንቃቄ ካልተያዘ ህይወት እስከማሳጣት የሚያደርስ መሆኑን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
እንደ አብነትም በተለያዩ ጊዜ በሀገራችን ቤት ዘግተው ጭስ እያጨሱ የሚተኙ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ማንሳት ይቻላል፡፡
እንደ አሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል መረጃ ÷ የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ በአይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ ነው፡፡
 
ካርበን ሞኖክሳይድ የሚፈጠረው ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው የሚፈጠር ሲሆን ÷ የእንጨት ከሰል ፣ የመኪና ጭስና ሲጋራ ይህንኑ በማመንጨት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሰልን ጨምሮ የካርበን ምንጭ የሆኑ እንደ ጋዝ ስቶቭ፣ ውሃ ማሞቂያ፣ የቤት ማሞቂያ፣ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች በሙሉ በአግባቡ ካልተገጠሙ፣ በአግባቡ ካልተጠገኑና ነፋስ የማያገኛቸው የተጨናነቀ ቦታ ከተቀመጡ ችግሩን ሊያከትሉ ይችላሉ፡፡
የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ ወደ ውስጣችን በምንስበብት ወቅት በቀጥታ በደማችን ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ሕዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለለተያዩ የሰውነታችን ክፍል ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ካርበኦክሲሄሞግሎቢን ይሆናል፡፡
ይህ ከሆነ በኃላ ደማችን ኦክሰጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ ሕዋሳቶቻችንና የሕዋሳቶቸችን አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ይሞታሉ፡፡
በከሰል ጭስ ወይም በካርበን ሞኖክሳይድ መጠቃታችንን የሚያሳዩ ምልክቶ-፡
መካከለኛ ለሆነ በጭሱ መጠቃት ውጥረት የተሞላ የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስ መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ ትኩረት ማጣት፣ የሆድ ሕመም፣ በአጭር መተንፈስና ለመተንፈስ መቸገር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድን መከላከያ መንገዶች-፡
• ማንኛውም ከሰል ምግብ ለማብሰል ስንፈልግ ከቤት ውጪ ማብሰል
• ከውጭ ማብሰል ካልቻልን ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱን ብቻ አረጋግጠን ወደ ቤት ማስገባት
• ቤት ያስገባነው ከሰል ምድጃ ነፋስ በስፋት በሚያገኝበት ቦታ ማድረግ
 
ምንጭ÷Hakim-bet.com
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.