Fana: At a Speed of Life!

ካናዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት በቶኪዮ ኦሊምፒክ እንደማትሳተፍ አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ካናዳ በጃፓን ከሚካሄደው የ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ራሷን ማግለሏን አስታወቀች።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በሃገራቸው አስተናጋጅነት የሚካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ በኋላም ካናዳ በውድድር ላይ እንደማትሳተፍ አስታውቃለች።

ውሳኔው የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖች እና መንግሥት ጋር ካደረገው ውይይት በኋላ የተላለፈ ነው ተብሏል።

በተያያዘም አውስትራሊያ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ውድድሩ ሊራዘም ይችላል በሚል አትሌቶቿ ለቀጣዩ ዓመት ውድድር እንዲዘጋጁ መልዕክት አስተላልፋለች።

የቶኪዮ ኦሊምፒክ በቀጣዩ ሐምሌ ወር ላይ እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.