Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ በሶማሊያ ላይ ጥላው የነበረውን የቀጥታ በረራ እገዳ አነሳች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ኬንያ በሶማሊያ ላይ ጥላው የነበረውን የቀጥታ በረራ እገዳ ማንሳቷን የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እርምጃው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደነበረበት ይመልሰዋል የሚል ተስፋ እንዳለው ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ተጓዦች ከኮቪድ 19 ነጻ የሆኑበትን ሰርተፊኬት ጨምሮ አሁን ያሉትን የበረራ ፕሮቶኮሎች ማሟላት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ መሃመድ ኢብራሂም በበኩላቸው፥ በኬንያ ወሳኔ ደስታቸውን ገልጸው፤ እርመጃው የሁለቱን ሃገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ መንገድ ይከፍታል ሲሉ በውሳኔው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኬንያ ወደ ሶማሊያም ሆነ ከሶማሊያ ወደ ኬንያ የሚደረጉ በረራዎችን ያገደችው በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.