Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ 20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የተመዘበሩ ንብረቶችን አስመለሰች

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ 20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የተመዘበሩ ንብረቶችን ማስመለሷ ተገለጸ።

ተመላሽ የተደረጉት ንብረቶች በሀገሪቱ ባለስልጣናት እና የመንግስት ሰራተኞች በሙስና የተመዘበሩ መሆናቸውን የኬንያ ዓቃቤ ህግ አስታውቋል።

የሀገሪቱ ዓቃቤ ህግ ኑረዲን ሃጂ እንደገለጹት፥ በቅርብ አመታት ውስጥ ከመንግስት ካዝና በሙስና የተሰረቁ ንብረቶችን የማስመለሱ ተግባር በትኩረት እየተሰራበት ነው።

በዚህም እስካሁን 20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ በተለያየ የሙስና መንገድ ተመዝብረው የነበሩ የመንግስት ንብረቶች ማስመለስ መቻሉን ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ ተመላሽ የሆነው ንብረት ሀገሪቱ በተለያዩ የሙስና መንገዶች ካጣችው ሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ውስጥ አንድ በመቶው ብቻ መሆኑን ነው የገለጹት።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አስታውሰዋል።

ኬንያ የመንግስት ንብረት በከፍተኛ ደረጃ በሙስና ከሚመዘበርባቸው ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይነገራል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.