Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የማንቼስተር ዩናይትድ ዝውውሩን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ የማንቼስተር ዩናይትድ ዝውውሩን አጠናቀቀ።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች የላንክሻየሩን ክለብ በይፋ የተቀላቀለ ሲሆን፥ ለዝውውሩም 19 ነጥብ 8 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ በክለቦቹ መካከል ስምምነት ተደርሷል።

ከዚህ ውስጥ 12 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንዱ በቀጥታ የሚከፈል ሲሆን፥ ቀሪው ገንዘብ በቆይታው እየታየ የሚጨመር መሆኑን የደይሊ ሜይል ዘገባ ያመላክታል።

ሮናልዶ ዳግም በተቀላቀለው የቀድሞ ክለቡ በሳምንት 385 ሺህ ፓውንድ ክፍያ የሚያገኝ ሲሆን፥ ለአንድ አመት ተጨማሪ የማራዘም አማራጭ ያለው የሁለት አመት ኮንትራት ተፈራርሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.