Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

በኮሚሽኑ የአሶሳ አስተባባሪ ቪክቶሪያ ኮፓ ድጋፉን ዛሬ በአሶሳ ከተማ ለክልሉ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡

አስተባባሪዋ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ኮሚሽኑ የመተከልን ተፈናቃዮች ለመደገፍ ከክልሉ ጋር በመቀናጀት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከድጋፉ መካከልም 13 ሺህ ብርድ ልብሶች እንዲሁም የአልጋ አጎበሮች፣ ምንጣፎች፣ የተለያዩ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ይህም ከአራት ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ነው አስተባባሪዋ የገለጹት፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ÷ በመተከል ዞን የተፈናቀሉትን ወገኖችን በመንግስት አቅም ብቻ ለመደገፍ አዳጋች በመሆኑ መንግሥት ኀብረተሰቡን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ረጂ ድርጅቶችም እንዲያግዙ ጥሪ መቅረቡን አስታውሰዋል፡፡

ጥሪውን ተቀብሎ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሰጠው ምላሽ ም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ በዞኑ በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት ቡለን እና ድባጤ ወረዳዎች በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚደርስ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.