Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የተጣለበትን ሃገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ምክትል ከንቲባዋ ኮሚሽኑ ከወሰን፣ ከማንነት እና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚያሰራው የጥናትና ምርምር ስራ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከአስተዳደር ወሰን ከማንነትና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር ተያይዘው እየተነሱ ላሉ ጥያቄዎች መፍትሄ ሊሆን የሚችል ምክረ-ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስራውን ውጤታማ ለማድረግም የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ጥናትና ምርምሩ ሃገር አቀፍ እንደመሆኑ መጠን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰኑ ክፍለ ከተሞች በናሙናነት ተመርጠው ጥናት እየተካሄደባቸው መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.