Fana: At a Speed of Life!

ኮሚቴው በመተከል ዞን የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላልፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ ብሔራዊ ኮሚቴ በህግ ማስከበር ሂደቱ ለተከሰቱ ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ተግባራትን ለመገምገም መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዚህም በመተከል ዞን የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንዲቋቋም ውሳኔ ተላልፏል።
የሚኒስትሮች ኮሚቴው የዕለቱ ተቀዳሚ አጀንዳዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ እርዳታ የማዳረስ ተግባራትን ገምግሟል።
እንዲሁም በትግራይ ክልል እና አጎራባች የአማራና አፋር ክልሎች ህግ ለማስከበር ከተወሰደው እርምጃ በኋላ ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ እና በዘላቂነት የመልሶ የማቋቋም ተግባራትን ሂደትንም ገምግሟል።
በሰላም ሚኒስቴር የሚመራው የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን፣ እና ሌሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ አካላትን የያዙ ቡድኖች በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር ክልሎች እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ይገኛሉ።
በቡድኖቹ የተጠናቀሩ የየዕለት ተግባራት ሪፖርቶችና የኮሚቴው አባላት አመራሮች በቦታው ተገኝተው ባደረጓቸው የመስክ ምልከታ ላይ ተመስርቶ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በብሄራዊ አደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን አስተባባሪነት በመተከል ዞን በቅርቡ በተመሰረቱት ካምፖች ለሚገኙ ወገኖች የዕለት ደራሽ እርዳታ ማከፋፈሉ እንደቀጠለ ሆኖ በተጨማሪም በርካታ የዕለት ደራሽ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪኖች ወደቦታው መንቀሳቀሳቸውን ኮሚሽኑ ገልጿዋል።
ኮሚቴው በመተከል ዞን የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታዎች የሚመራ ግብረ `ኃይል በቦታው ተገኝቶ ለማስተባበር እንዲሁም እንደየአስፈላጊነቱ አመራርና ውሳኔ ለመስጠት ወደ መተከል ዞን ተጉዟል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.