Fana: At a Speed of Life!

ኮሚቴው በሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ እና የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ ተግባራትን ላይ በመምከር አቅጣጫ አስቀመጠ።

ኮሚቴው በህግ ማስከበር ሂደቱ ለተከሰቱ ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ ተግባራትን እንዲሁም የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት አካሂዷል።

ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በትብብር እየተከናወኑ ያሉ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትም ቀርቧል።

በብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ድጋፍ የክልል ድንገተኛ ማስተባበሪያ ማዕከላት ቀደም ሲል በዳሰሳ ጥናት የተለዩ ፍላጎቶችን የማሟላት ተግባራትን ከሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮች ጋር በቅንጅት እያከናወኑ እንደሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ በቀጣይ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት የተለዩ ሲሆን የኮሚቴው ሰብሳቢ የሰላም ሚኒሰትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቀጣይ ስራዎች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.