Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ለሲኤምሲ የመኖሪያ መንደር ነዋሪዎች የገነባውን የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን እድሳት ሥራ እና በሲኤምሲ የመኖሪያ መንደር የከርሰምድር የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አጠናቆ በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በዚህ ወቅት ÷ ኮርፖሬሽናችን አገራዊ ለውጡን መሰረት በማድረግ ውጤታማ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የሲኤምሲ መኖሪያ መንደር የከርሰምድር የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በ2007 ዓ.ም የውጭ ኮንትራክተር ውል ወስዶ ስራውን ቢጀምርም አጠናቆ ማስረከብ እንዳልቻለም ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ኮርፖሬሸኑ እያካሄደ ባለው ውጤታማ ተቋማዊ ሪፎርም ምክንያት በገነባው የመፈጸም አቅም በራስ ዓቅም ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለመኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ለአገልግሎት ማብቃት ተችሏል ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

ያልተጠናቀቀውን የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የውጭ ኮንትራክተር በ9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ለመስራት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም በራስ አቅም በመሰራቱ ግንባታውን በ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በማጠናቀቅ 6 ሚሊየን ብር ማደን መቻሉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ከራስ አልፎ ለውጭ ተቋማት መሰል ሥራዎችን በማከናወን ተጨማሪ ገቢ ኮርፖሬሽኑ ማግኘት የሚችልበትን እድል መፍጠር መቻሉንም መናገራቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.