Fana: At a Speed of Life!

ኮሮና ቫይረስ በቆዳ ላይ 9 ሰዓት እንደሚቆይ አንድ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ኮሮና ቫይረስ በሰው ልጅ ቆዳ ላይ ዘጠኝ ሰዓት እንደሚቆይ አንድ ጥናት አመላክቷል፡፡

ይህም ቫይረሱ ከጉንፋን አምጭው ቫይረስ አምስት እጥፍ የሚረዝም ጊዜ በሰው ልጅ ቆዳ እንዲቆያ ያደርገዋል ሲሉ የጃፓን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡

አዲሱ የምርምር ውጤት እጅን አዘውትሮ መታጠብ ቫይረሱን ለመከላከል ይረዳል የሚለውን የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሃሳብ የሚደግፍና የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡

ጉንፋንን የሚያስከትለው ቫይረስ በሰው ቆዳ ላይ በንፅፅር ለ1 ነጥብ 8 ሰዓት ያህል በሕይወት እንደሚቆይ ጥናቱ አመላክቷል፡፡

የጉንፋን እና የኮሮና ቫይረስን ኢታኖል በተቀላቀለበት የእጅ ማጽጃ በመጠቀም በ15 ሰከንድ ውስጥ ከሰውነት ቆዳ ማስወገድ ይቻላል ነው የተባለው፡፡

እስካሁን በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40 ሚሊየን የተጠጋ ሲሆን በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ1 ሚሊየን 119 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

በአንጻሩ ከቫይረሱ ከ30 ሚሊየን 156 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.