Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ19 በአውሮፓ እየተስፋፋ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮቪድ19 ቫይረስ ምክንያት በአውሮፓ አገራት ሕይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በ10 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

አውሮፓ ከሌሎች ክፍለ ዓለማት በተለየ መልኩ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭት እና በቫይረሱ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የሄደበት አህጉር ሆኗል፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት ጤና ኤጀንሲ ሣምንታዊ ሪፖርት ደግሞ፥ በሣምንቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች ኮቪድ19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ያህሉ የተመዘገቡት ከአውሮፓ መሆኑን አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

በአውሮፓ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክላጅ፥ “አውሮፓ እንደገና የኮቪድ19 ወረርሽኝ ማዕከል ሆናለች ፤ ቫይረሱን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ወር 500 ሺህ ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ” ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.