Fana: At a Speed of Life!

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 526 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 526 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያስመረቃቸው ተማሪዎች በቀን፣ በማታ፣ በርቀት፣ በክረምት እና በቅዳሜ እና እሁድ ቀናት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ምሩቃኑ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማስተርስ እና በዲፕሎማ የሰለጠኑ ሲሆን÷ 1ሺህ 285 ወንዶች እና 1 ሺህ 241 ሴቶች ናቸው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ሌሎች የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

“ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ” ስሙ ወደ “ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲቀየር መወሰኑን ኢዜአ አስታውሶ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.