Fana: At a Speed of Life!

ኳታርና ግብፅ ለ3 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና ለማስጀመር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ኳታርና ግብፅ ለ3 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና ለማስጀመር ተስማሙ።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸውን የነበረውን የሁለትዮሽ ዲሎማሲያዊ ግንኙነት በድጋሜ ለማስጀመር የመግባቢያ ስምምነት ተለዋውጠዋል ብሏል።

የሁለትዮሹ ስምምነት የመጣው ኳታር ብቻዋን እና ሳዑዲ አረቢያ ፣ ግብፅ ፣ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በጋራ የነበራቸውን ልዩነት ለመፍታት ስምምነት ላይ ከደረሱ ሳምነት በኋላ ነው።

ግብፅ ስምምነቱን የአረብ ሀገራትን ተግባራት ለማጠናከር እና የአካባቢውን ግንኙት ለማጠናከር ያስችላል ስትል  መግለጿን ሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.