Fana: At a Speed of Life!

“ኸርድ ኢሚዩኒቲ”ን መምረጥ የስነ ምግባር ችግር ነው – ዶክተር ቴዎድሮስ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ እንዲያዙ በማድረግ በሽታ የመከላከል አቅምን ማዳበር (ኸርድ ኢሚዩኒቲ) ጥቅም ላይ ማዋልን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አጣጣሉ።
ኸርድ ኢሚዩኒቲ ሊፈጠር የሚችለው ክትባት በመውሰድ እና በሽታዎች በሚስፋፉበት ወቅት በርካታ ህዝብ በሽታ የመከላከል አቅም ሲያዳብር መሆኑ ይነገራል።
አንዳንድ አካላትም ምንም አይነት ክትባት ሳይኖር የኮሮና ቫይረስ ተፈጥሯዊ ስርጭት እንዲኖረው ማድረግ ይገባል ይላሉ።
በትናንትናው ዕለት ዳይሬክተሩ በሰጡት መግለጫ ኸርድ ኢሚዩኒቲ በሳይንስም ሆነ በስነ ምግባር ችግር ያለበት ነው ብለዋል።
ዶክተር ቴድሮስ የኮሮና ቫይረስ በረጅም ጊዜ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅም ምላሽ ጥንካሬ እና የጊዜ ቆይታ አሁንም ያልታወቀ ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኸርድ ኢሚዩኒቲ አቅምን ማሳደግ የሚቻለው ሰዎችን ለቫይረሱ በማጋለጥ ሳይሆን ከቫይረሱ በመከላከል መሆኑን ገልፀዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ ከተከሰተ ጀምሮ 37 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቁት ዶክተር ቴድሮስ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል ነው ያሉት።
አሁን ላይ ከ100 በላይ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች እየተዘጋጁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በተሻለ የሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ነገር ግን ከእነዚህ ክትባቶች ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማረጋገጫ ያገኘ የለም።
ምንጭ፥ ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.