Fana: At a Speed of Life!

ወላጆቻችን በነጻነት ያቆይዋትን አገር ከወራሪዎች መጠበቅ አለብን – ሜ/ጄ ጥሩዬ አሠፌ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥንት አባቶቻችን ሉዓላዊነቷን አስከብረውና ነፃነቷን አስጠብቀው ያስረከቡንን አገር በእኛ ዘመንም ከዘራፊዎችና ከወራሪዎች የመጠበቅ ግዴታ አለብን ሲሉ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሠፌ ተናገሩ፡፡

በመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች በአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሴቶች ሚና ምንድን ነው? በሚል ርዕሰ ጉዳይ ውይይት አካሂደዋል ፡፡

የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሠፌ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት፥ ከጥንት አያቶቻችን ጀምሮ አገር ስትወረር ሴቶች የመረጃ ምንጭ በመሆን ፣ በማህበራዊ ፣ በፖለቲካዊ እና ለዘማቾች ሞራል በመስጠት የማነቃቃት ሥራ ሲሰራ ቆይተዋል፡፡

በተቋም ደረጃም በርካታ ሴት የሠራዊት አባላትና ጀግኖች በአዋጊም በተዋጊም ደረጃ ያሉ ሲሆን በተሠማሩበት የስራ መደብ ሁሉ አመርቂ ውጤት እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአገራችን በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱ ዜጋ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ቢሆንም ለሠራዊት ደግሞ ድርብ ኃላፊነት ስለሆነ ሴት ሠራዊቶችም እያንዳንዷን ሂደት በአግባቡ ለመጠቀም የህልውና ዘመቻውን በመደገፍና በመሳተፍ አጋዥና አርአያ መሆን አለብን ብለዋል፡፡

በመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት የፋይናንስ ዘርፍ ዳይሬክተር ኮሎኔል አሠለፈች ጎቸል በበኩላቸው፥ ሴት የሰራዊት አባላት በማንኛውም የሥራ መስክ ተወዳዳሪ ለመሆን ራሳችንን በትምህርት እና ሥልጠና ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል ፡፡

በመከላከያ ሚዲያ የሬዲዮ ቡድን የመዝናኛ ዴስክ መሪ ሻለቃ ፍቅርተ አለማየሁ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት የአገራችንን እውነት የምንገልፅበትና የሠራዊቱን ጀብዱ እና ገፅታ የምናሳይበት ስለሆነ ሁሉም ሠራዊት የሚጠበቅበትን ሁሉ በማድረግ አገርን ማስቀጠልና ሉዓላዊነቷን ለትውልድ ማስረከብ አለብን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.