Fana: At a Speed of Life!

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለተፈናቃዮች ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በደባርቅ እና ዳባት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 4 ሚሊየን 284 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
 
የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጭልጋና አካባቢው ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ጌታሁን እንደገለጹት÷ድጋፉ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅና ዳባት መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ አባውራና እማውራዎች ነው የተደረገው፡፡
 
ድርጅቱ በሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የጥሬ ገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዳደረገም ገልጸዋል።
 
ከመንግሥትና ከተፈናቃዮች ጋር በመሆን ተጠቃሚዎችን በትክክል ለመለየት ጥረት እንደተደረገ መሆኑን መጥቀሳቸውንም ከሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ተፈናቃዮች በበኩላቸው ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው÷ድርጅቶች፣ መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.