Fana: At a Speed of Life!

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ ሩብ ቢሊየን ብር መድቤ እየሰራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ከተማ በአሸባሪው ህወሓት ቡድን የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ ወርልድ ቪዥን ለችግሮቹ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ሳሙኤል እንደገለፁት ÷ የምግብ እና የንፁህ መጠጥ ውኃ እጥረት፣ የፈረሱ ቤቶችን ለማደስ እና የፋብሪካ ምርቶችን ለማቅረብ ሩብ ቢሊየን ብር ተመድቦ እየተሠራ ነው።

እስካሁን 50 ሚሊየን ብር ከጭልጋ ለተፈናቀሉ፣ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው እና በደሴ እና በደባርቅ ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ በጂሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፉርሲ፣ በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፣ በአጣዬና ሸዋሮቢት፣ በጭልጋና በላይ አርማጭሆ አካባቢዎች ይተገበራሉ ተብሏል።

በሰሜን ወሎ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስድስት ወረዳዎች የ21 ሚሊየን 548 ሺህ ብር ፕሮጀክት የትውውቅ መርሃ ግብርም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

ፕሮጀክቱ ለሴቶችና ሕፃናት ግልጋሎት እንደሚሰጥ ተገልጾ ÷ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከተፈናቀሉና ከተጎዱ ዜጎች ጎን በመቆም ይህን ክፉ ጊዜ ተባብሮ ማለፍ እንደሚገባ አቶ ሳሙኤል ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.