Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች በአዲስ አበባ በሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ሊዮ ዩሺ ጋር በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች እና ተያያዥ የትብብር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ።

ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በውይይታቸው የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ /ሲ.ዲ.ሲ/ ዋና መስሪያ ቤትን ዕውን የማድረግ የትብብር አቅጣጫ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና የአህጉሪቱ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ማዕከል ከተማ መሆኗን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባዋ ደረጃቸውን የጠበቁ ስራዎችና ፕሮጀክቶችን በትብብር መስራንት እንቀጥላለን ብለዋል።

የአፍሪካ መንደር ፕሮጀክት እና የሲ.ዲ.ሲ አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንዲገነቡ በማድረግ ረገድ ላደረጉት አስተዋጽኦም በከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና መስሪያ ቤት የመሠረተ ድንጋይ ባለፈው ሳምንት የተቀመጠ ሲሆን በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የማዕከሉ ህንጻ ወጪው በቻይና መንግስት የሚሸፈን መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.