Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች አበቤ ላለፉት 7 ዓመታት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ ስራ ያልተጀመረባቸውን የሁለት ጠቅላላ ሆስፒታሎች ግንባታ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ላለፉት ሰባት ዓመታት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ ስራ ያልተጀመረባቸውን ሁለት አጠቃላይ የሆስፒታል ግንባታ ስራዎች በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች የሚገነቡት ሆስፒታሎች እያንዳንዳቸው ከ548 ሚሊየን ብር በላይ በጀት እንደተያዘላቸው በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ላይ ተመልክቷል።

የአጠቃላይ ሆስፒታሎቹ ግንባታ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ሆስፒታሎቹ የሪፈራል አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው ከክፍለ ከተሞቹ ውጭ ከምዕራብ፣ ከደቡብ ምዕራብ እና ከምስራቅ ኦሮሚያ ለሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት ይሰጣሉ ነው የተባለው።

የአካባቢው ማህበረሰብ የሚያነሳውን የሆስፒታል አገልግሎት ተደራሽነት ችግር ለመፍታት እና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሎቹ ዓይነተኛ ሚና እንደሚወጡ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ላለፉት ሰባት ዓመታት የሆስፒታሎቹን ግንባታ በትግእስት ለጠበቀው የህብረተሰብ ክፍል ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ከንቲባዋ፥ ማንኛውም ፕሮጀክት የሚጀመረው ለማጠናቀቅ ነው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.