Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች በመስቀል አደባባይ የመንገድ ዳር ብረቶችን የኬሚካል የመርጨት ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ጉሜን 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የይቅርታ ቀንን በማስመልከት በመስቀል አደባባይ በመገኘት የመንገድ ዳር ብረቶችን የማጽዳት እና ኬሚካል የመርጨት ስራ አከናውነዋል።

የጽዳት ዘመቻው የይቅርታ ቀንን በማስመልከት ህብረተሰቡ እራሱን ከቂም እና አከባቢውን ከቆሻሻ ማጽዳትን አላማ ያደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ አከባቢያችንን ከቆሻሻ ፤ ውስጣችንን ከጥላቻ እናፅዳ ሲሉ ተናግረዋል ።

የከተማችን ነዋሪዎች በአካልም ፣በመንፈስም ከሚያራርቀው ጥላቻ ተላቅቀው በህብረት ለመሻገር ይቅርታ እንዲደራረጉ እና አከባቢያቸውንም እንዲያጸዱ አሳስበዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች ነጋሽን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.