Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ዳግማዊት በአየር ብክለት በሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ስለዓለም አቀፍ የአየር ብክለት በሚመክር ጉባኤ ላይ ተወያዩ፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ውይይት ላይ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አፍሪካን በመወከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የአየር ብክለት ጉባኤ ላይ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

የካርበን ልቀትን በመቀነስ የአየር ብክለትን በመቆጣጠር ረገድ የትራስፖርት ዘርፍ መጠቀም የሚችላቸውን አማራጭ ሀሳቦች አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ የዚህ እንቅስቃሴ አካል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ባለፋት ዓመታት እያከናወነች ያለውን በርካታ ጥረት በጉባዔው ላይ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ በትራንስፖርት ዘርፍ የካርበን ልቀት በሚቀንስበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብትና የፈጠራ ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ገልጸው በኢትዮጵያ በቅርቡ በጸደቀው የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይዘትና ተግባራዊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በጥቅሉ የትራንስፖርት ዘርፋን እንቅስቃሴ በማሻሻል የእግርና የብስክሌት ጉዞን በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ ለአየር ብክለት ምክንያት ባለመሆን ሊሰራ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመድረኩ ላይም የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የበርካታ ባለድርሻ አካላትና መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የጉባዔው ዋና አላማ ከአምስት ዓመታት በፊት ይፋ በሆነው ለአየር ንብረት ለውጥ በተዘጋጀው የፖሪስ ስምምነትን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከትራንስፖርት ዘርፉ እየጨመረ የመጣውን የካርበን ልቀት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በቀጣይ ዓመታት ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራትን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.