Fana: At a Speed of Life!

ወደ መቀሌ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች ልዑካን ቡድን የህዋሃትን የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው – ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ መቀሌ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች የልዑካን ቡድን የህዋሃትን የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተትነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ መንግሰት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም ስምምንት ለማድርግ ወሰኖ እንደነበር እና አሁንም ለሰላም ውይይት ፍላጎት ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የምግብ ድጋፍ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

ይሁን እንጂ መንግስት ወደ ትግራይ የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ ባላቋረጠበት እና ክልከላዎች ባላደረገበት ወደ መቀሌ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኞችን የያዘው የዲፕልማቶች ቡድን የህዋሃትን የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚካሄደው የሰላም ውይይት ሁሌም በማንኛውም ቦታ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንዳሳየ ጠቁመዋል።

ነገር ግን በህዋሃት በኩል ከሰላም ድርድር ፍላጎት ይልቅ አሁንም የጦርነት ጉሰማዎች እና ለሰላም ውይይት እንቅፋት የሚሆኑ ንግግሮች እየተሰሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.