Fana: At a Speed of Life!

ወደ አማራ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንዳይገባ እገዳ ተጣለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትናንት ጀምሮ ወደ አማራ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንዳይገባ እገዳ ተጣለ።

ከሀገሪቱ የትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል የሚጓዙ ማናቸውም ዓይነት የሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከልከሉን የአማራ ክልል መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

ከዩኒቪርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው እየመጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ግን በልዩ ሁኔታ የሚገቡ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ መግለፁን አብመድ ዘግቧል።

ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆንም ለፀጥታ አስከባሪ ኃይል ትዕዛዝ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.