Fana: At a Speed of Life!

ወደ አፋን ኦሮሞ እየተተረጎመ ባለው የቋንቋ ፖሊሲ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አፋን ኦሮሞ እየተተረጎመ ባለው የቋንቋ ፖሊሲ ላይ ሰኞ ዕለት በኦሮሞ ባሕል ማዕከል ውይይት መካሄዱ ተገለጸ፡፡

ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ 5 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የፌዴራል መንግስት የሥራ ቋንቋ ሆነው እንዲያገለግሉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡

በውይይቱ በሀገራችን ተጨማሪ 5 ቋንቋዎች የፌዴራል መንግስት የሥራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ የቋንቋ ፖሊሲውን ወደ አፋን ኦሮሞ መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

የፖሊሲ ትርጉም ሥራውን ለማስጀመር የጥናትና ምርምር ኢኒስቲትዩት ከኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር የቋንቋ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦሮሞ ባሕል ማዕከል አድርገዋል፡፡

የቋንቋ ፖሊሲውን በጥንቃቄ ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለመተርጎም የቋንቋ ምሁራን ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ ቡጤ ገልጸዋል፡፡

የቋንቋ ምሁራኑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ እንደሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

በ ደጀኑ ጎንፋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.