Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል አብዱላህ ጋር በስደት የሚገኙ ወገኖችን ወደ ሀገራቸው መመለስና በዘላቂነት ማቋቋም በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ የእህትማማችነት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል፡፡
እንዲሁም በዋነኝነት በስደት የሚገኙ ወገኖችን ወደ ሀገራቸው መመለስና በዘላቂነት ማቋቋም ላይ መወያየታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.