Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የአሜሪካን ተራድኦ ድርጅት  ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የአሜሪካን ተራድኦ ድርጅት (USAID Ethiopia) ሚሽን ዳይሬክተር  ሾን ጆንስ ጋር በአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቅ ስርዓት እና በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ሀገራት የተለያየ ልምድ ያላቸው በመሆኑ የአሰራር ለውጡን የማያዳግም ለማድረግ ከተለያዩ ሀገራት ልምድ መቅሰም አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም አጋሮች ከአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሰጭነት ጎን ለጎን የቅድመ ማስጠንቀቅ ስርዓት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራርን የማዘመን የለውጥ ሂደት ላይ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በወቅቱም  ሚኒስትሯ  ሊከሰቱ የሚችሉ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል እንዲሁም ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ሰጭነት ባለፈ የዘመነና የተቀናጀ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቅ  እና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ፈጣን ምላሽ ስርዓት ላይ የአሰራር ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የተጀመረ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቅ ስርዓት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ለውጥ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል።

ዳይሬክተሯ በበኩላቸው የተጀመረውን ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ ሂደት በእጅጉ የሚደገፍና እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም  የልምድ ልውውጥ ማድረግን ጨምሮ ማንኛውንም አስፈላጊ እገዛ ለማድረግ ድርጅታቸው ቁርጠኛ መሆኑን  ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ የአሜሪካን መንግስት እና ህዝብ እስከ አሁን ሲያደርጉ ለነበረው ባለብዙ ዘርፍ ድጋፍ እንዲሁም በቀጣይም በተለይም የአደጋ ዝግጁነትና ፈጣን ምላሽ ስራ አመራርን ለማዘመንና የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ የሚደረገውን የለውጥ ርብርብ ለማገዝ እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ ለሚደረገው ትብብርና ለተገባው ቃል ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.