Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተመድ የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተመድ የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ጸሀፊ ሮዝሜሪ ዲያካርሎ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ዋና ፀሀፊን ፓርፌት ኦናጋ አናያንጋን እና የተመድ የነዋሪዎችና እና የሰብዓዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት፥ የሰላም ሚኒስቴር ከተቋቋመ ጀምሮ እያከናወናቸው ያሉ ዋና ዋና ተግባራትን በማብራራት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በፊት የነበረውን አሉታዊ ሰላም ወደ አወንታዊ ሰላም ለመቀየር ሰፊ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፉ ትልልቅ ለውጦችን እያመጣች ትገኛለች ያሉት ሚኒስትሯ፥ የሰላም ግንባታ ስራውም ትልቀ ትኩረት እንደተሰጠው ገልፀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር በሀገሪቱና በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና የሰላም ግንባታ ስራውን በዘላቂነት ለማስቀጠል ትኩረት የሚያደርገው በማህበራዊ ሃብቶች ላይ ነው ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት፥ በኢትዮጵያ ለሰላም ግንባታ ስራ የሚውሉ በርካታ ተሞክሮዎችና ልምምዶች እንዳሏትም አስታውቀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን ጨምር በሀገር ደራጀ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ወደ ተግባር መግባቱን መግለፃቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ዋና ዓላማውም በሰላም ባህል ግንባታ ላይ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ነው እንደሆነም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አስታውቀዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ጸሀፊን ዲያካርሎ በበኩላቸወ ኢትዮጵያ በሰላም ባህል ግንባታ ላይ ትልቅ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.