Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑዌላ ዴል ሬ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑዌላ ዴል ሬ ጋር የስልክ ውይይት አካሂደዋል።
ሚኒስትሯ በህወሓት ጁንታ ላይ ሲካሄድ የነበረው ህግ የማስከበር ተግባር መጠናቀቁን እና በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ስላለው ትብብር ገለፃ አድርገዋል፡፡
የሕግ ማስከበር ሥራው ሲቪሎችንና መሠረተ ልማቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ እጅግ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መከናወኑንም ገልፀዋል።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በበኩላቸው በሕግ ማስከበር ሂደት ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የተደረገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን የጣሊያን መንግስት በኢጣሊያ የቀይ መስቀል ማህበር አማካይነት በተለይ የህክምና ግብዓቶችን በማቅረብ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የወዳጅነት ግንኙነትም የበለጠ እንደሚጠናከር አረጋግጠዋል ፡፡
ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የጣሊያን መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ለመረዳት ችለናል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.