Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የአትክልት መገበያያ ስፍራን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የአትክልት መገበያያ ስፍራን ጎበኙ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የአትክልት መገበያያ ስፍራ የግንባታ ሂደትን ተዘዋውረው የጎበኙት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተገነቡ ያሉ አብዛኛው የመገበያያ ሼዶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ተመልክተዋል፡፡

ከቀጣይ ሳምንት በኋላም በጃንሜዳ የሚገኙ የአትክልት ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ የማንሳት ስራ እንደሚሰራ ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የአትክልት የገበያ ማዕከል 80 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚገነቡት 14 ሼዶች እያንዳንዱ ሼዶች 70 ሜትር በ6.6 ሜትር ስፋት 588 የመገበያያ ሱቆች እንደሚኖሩት ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.