Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 49 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ አምስት የመንገድ ፕሮጀክቶችን ስራ በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 49 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ አምስት የመንገድ ፕሮጀክቶችን ስራ በይፋ ማስጀመራቸው ተገለጸ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና አፈጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እንዲሁም የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የካቢኔ አባላት በተገኙበት ፕሮጀክቶች በይፋ ስራ እንዲጀመሩ ተደርጓል፡፡

በዚሁ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው በጀት ዓመት ከ280 ኪሎሜትር በላይ መንገድ ስራ እንደሚጀመር ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ዛሬ በይፋ ስራቸው እንዲጀመር ከተደረጉት ፕሮጀክቶች መካከል አራቱ በኮዬ ፈጬና ቱሉዲምቱ የጋራ መኖሪያ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን አንደኛው ከሲኤምሲ ወደ ጎሮ የሚወስድ የመንገድ ፕሮጀክት ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ እንደገለፁት በ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 49 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ እና ከ15 እስከ 40 ሜትር የጎን እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከአንድ ዓመት ከሰባት ወር እስከ ሁለት ዓመት ባለው ግዜ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ መገለጹን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.