Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
 
የወዳጅነት ጨዋታው ጥቅምት 12ና 15 ቀን 2013 በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው።
 
ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅቱን በካፍ አካዳሚ እያከናወነ የሚገኘ ሲሆን ከኒጀር ጋር ከሚያደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ በፊት ነው የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያከናውነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.