Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን አቻው ጋር ተጫውቷል፡፡
 
ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
 
የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ጌታነህ ከበደ ባስቆጠራት ጎል በዋልያዎቹ መሪነት ቢጠናቀቅም ሱዳኖች በተከታታይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ሲመሩ ቆይተዋል፡፡
 
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አማኑኤል ገብረሚካኤል ባስቆጠራት ጎል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.