Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በአቻ ውጤት ተለያይተዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሌሴቶ በ20ኛው ደቂቃ በማክሀ ቱሜሎ አማካኝነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥራለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ አቻ የምታደርገውን ጎል በ61ኛ ደቂቃ በይገዙ ቦጋለ አማካኝነት አስቆጥሯል፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ሰኞ 10 ሰዓት ላይ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

ፎቶ -ሶከር ኢትዮጵያ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.