Fana: At a Speed of Life!

ውፍረት ካስቸገረዎት ይህን የቪዲዮ ጌም ይሞክሩት

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቪዲዮ ጌም እየተዝናኑ ውፍረት መቀነስን አስበውት ያውቃሉ?

ከወደ ፊሊፒንስ የተሰማው ዜና ስሜት በሚይዝ የቪዲዮ ጌም እየተዝናኑ ክብደት መቀነስ ይችላሉ ይላል።

ሚጊይ ገብርኤል የተባለው የግራፊክስ ባለሙያ “ኒንቴንዶ ሪንግፊት አድቬንቼር” ቪዲዮ ጌምን ለአንድ ወር ይጫወታል።

ግለሰቡ ጌሙን ለተከታታይ ቀናት በመጫወቱ ሰውነቱ ላይ ለውጥ ማምጣቱን ገልጿል።

ጌሙ እንደሌሎች ጌሞች ተቀምጠው የሚጫወቱት ሳይሆን እንቅስቃሴ የሚፈልግ መሆኑ ደግሞ ለክብደት መቀነስ ምክንያት መሆኑ ነው የተነገረው።

ሚጊይ “ይህን ጌም ለተከታታይ 30 ቀናት በመጫወቴ 9 ኪሎ ግራም በአንድ ወር ውስጥ እንድቀንስ አስችሎኛል” ሲል ደስታውን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለወዳጆቹ አጋርቷል።

ግለሰቡ የሰውነት ክብደት ለውጥ ማምጣቱን ለማረጋገጥም ከሳምንት በፊት እና በኋላ በማለት ፎቶዎቹን በፌስቡክ ገፁ ለጥፏል።

ከዚህ ቀደም የሰውነት ክብደቱን ለመቀነስ ብስክሌት ማሽከርከርን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ሲሰራ እንደነበር በመግለፅ በዚህ ለውጥ አለማምጣቱን ይገልጻል።

ቪዲዮ ጌሙን በየቀኑ ለ25 ደቂቃዎች በመጫዎት ለውጥ አምጥቻለሁ ሲልም ግለሰቡ ደስታውን ገልጿል።

ሚጊይ ከቪዲዮ ጌሙ ባለፈም በካርቦ ሀይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ መቆሙም ለክብደት መቀነሱ እንደረዳው አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.