Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ አልፏል።

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ በቫይረሱ ሳቢያ 102 ሺህ 782 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ከዚህ ውስጥ በጣሊያን እና አሜሪካ በተናጠል ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

በስፔን ደግሞ ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በአሜሪካ ከ2 ሺህ 100 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ይህም በአንድ ቀን የተመዘገብ ከፍተኛው የሞት መጠን ሆኗል።

1 ነጥብ 7 ሚሊየን አካባቢ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሲያዙ፥ ከዚህ ውስጥ በአሜሪካ ከ502 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

376 ሺህ 976 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.