Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተድሽነትን ለማሳካት ለያዘችው እቅድ 500 ሚሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያ በ2025 አለም አቀፍ አሌክትሪክ ለሁሉም ግብን ማሳካት እንድትችል አለም ባንክ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር (አይዲኤ) በኩል 500 ሚሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ።

ባንኩ ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በአሌክትሪክ ተደራሽነት እና አቅርቦት ላይ አበረታች ለውጦችን ማምጣቷን ነው የገለፀው።

ነገር ግን ከዚህ ስኬት ባሻገር አሁንም ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ በተለይ ለገጠሩ ማህበረሰብ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረብ እንዳልቻለች ባንኩ አስታውቋል።

ይህም የድህነት ሁኔታው እንዲቀጥል ፣ዜጎች መሰረታዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  ፍላጎቶቻቸውን እንዳያሳኩ እንዲሁም  አማራጮችን እንዳያገኙ ገድቧል ነው ያለው።

በመሆኑም የኢትዮጵያ የኤክትሪክ ብርሃን ተደራሽነት ፕሮጀክት የብሄራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት  ፕሮግራም ዋነኛ አካል እንደሆነ አለም ባንክ አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ 5 ሚሊየን ለሚጠጋ ህዝብ ፣ ለ11 ሺህ 500 ኢንተርፕራይዞች ፣ 1 ሺህ 400 ጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች ኤሌክትሪክን ለማቅረብ ያለመ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.