Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአፍሪካ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ ሊያጠናክር ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአፍሪካ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያጠናክር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በማላቦ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ15ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ቃል ኪዳን ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደገለፁት ÷የአፍሪካ ቀንድ በዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እና በድርቅ ሳቢያ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ከተከሰተባቸው ቀጠናዎች አንዱ ነው።

ይህንንም የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለመቀነስ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በቀጠናው የተከሰተው ተከታታይ ድርቅ እንደሚያሳየው ጠንካራ የአደጋ መከላከል እርምጃ ወሳኝ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርዓ-ግብር አገሪቱ በዓመት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል በሚቀጥሉት ጊዜያት በአየር ንብረት ለውጥ ሊመጣ የሚችለውን ፈተናዎች ለመቋቋም የጀመረችውን ሥራ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በዓለም የከፋ የኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበት እየታየ ቢሆንም ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ ሥደተኞች እና ከቄያቸው ለተፈናቀሉ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ መስጠቷን አጠናክራ ቀጥላለች ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአኅጉሪቱ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የሰብዓዊ እርዳታ ለማሳለጥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.